(EMF) በዛሬው እለት መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት፤ የግራዚያኒን ሃውልት መሰራት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል። ከታሰሩት መካከል ታዋቂው የህግ ሰው ዶ/ር ኃያዕቆብ ኃይለማርያም ይገኙበታል።
ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹ ከሁለት ቀናት በፊት የአዲስ አበባ አስተዳደር ጉዳዩን እንዲያውቅ በደብዳቤ ገልጸዋል። “…በቅርቡ የኢጣሊያ መንግስት ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ በማርሻል ግራዚያኒ ስም የመታሰቢያ ሙዚየም እና መናፈሻ መስራቱን በመቃወም ሰልፍ ጠርተናል። ስለዚህ የከተማው አስተዳደር ይህንን አውቆ በእለቱ የሚያስፈልገውን ትብብር እንዲያደርግልን እንጠይቃለ።” የሚል ደብዳቤ አስገብተው ነበር። ሆኖም መንግስት ትብብር ከማድረግ ይልቅ የሰላማዊ ሰልፉን አስተባባሪዎች እስር ቤት ወርውሯቸዋል። ለመረጃ እንዲሆን ለአዲስ አበባ አስተዳድር የላኩትን ደብዳቤ ለህትመት አብቅተነዋል።
No comments:
Post a Comment