Wednesday, 20 March 2013

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ አደረጉ




የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የትምህርት ማቆም አድማ ላይ እንዳሉ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡
እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ተማሪዎቹ በአመራር ላይ ያለው አስተዳደር ብቃት የለውም፣ የምግብ አቅርቦትና ጥራት ችግር አለ፤ ምላሽ ግን የሚሰጥም ሆነ ለማነጋገር ፈቃደኛ የሆነ አካል የለም በማለት የኮሌጁ የቀን ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ለማድረግ ተገደዋል፡፡ ተማሪዎቹ ለኮሌጁ አስተዳደር ካነሷቸው ጥያቄዎች በተጨማሪ፣ በኮሌጁ በርካታ ኃይማኖታዊ የአሰተዳደር ችግር እንዳለ ቢጠቅሱም በአስተዳደሩ ምላሽ አለመሰጠቱን ገልፀውልናል፡፡
በነዚህ ምክንያቶች ተማሪዎቹ ጥያቄዎቻቸው እስኪመለሱ ድረስ ትምህርት እንዳቆሙና አንዳንድ ተማሪዎችም መልቀቂያ (ክሊራንስ) እየሞሉ መውጣታቸውን የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ምንጮች  አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የማታ ተማሪዎችም  ከሐሙስ መጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ  ለኮሌጁ ደህንነት በሚል በአስተዳደሩ ትምህርት እንዲያቋርጡ መደረጋቸውን ተማሪዎቹ ለፍኖተ ነፃነት አረጋግጠዋል፡፡
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍልም የኮሌጁ ትምህርት የተቋረጠበትን ምክንያትና  ተማሪዎቹ አነሷቸው የተባሉትን ጥቄዎች በተመለከተ የኮሌጁን አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ሆኖም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ህዝቄልን ጠይቀናቸው “ትምህርት መቋረጡን ገና ከእናንተ አሁን መስማቴ ነው፤ የደረሰኝ መረጃ የለም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ምንም እንኳ ከጠቅላይ ቤተክህነቱ ዋና ፅህፈት ቤት እስከ ኮሌጁ ድረስ ያለው እርቀት በግምት ከ600 ሜትር ባይበልጥም የቤተክህነቱ ዋና ፀሐፊ ስለትምህርት ማቆም አድማው የሰሙት እንደሌለ ገልፀውልናል፡፡
ይህ መረጃ እስከተዘገበበት መጋቢት 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ በኮሌጁ ትምህርት እንዳልተጀመረ አረጋግጠናል፡፡
















በሲዊዲን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ



በስቶኮልም ሲዊድን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን የሰልፍ አስተባባሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም የተደረገው የተዋውሞ ሰልፍ አላማ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ መንግስት እያደረሰ ያለውን በደል ለመቃወም መሆኑን የገለፁት የሰልፉ አስተባባሪዎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ከ 200 በላይ በስቶኮልምና በአካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መገኘታቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
ሰልፉን ያስተባበሩት በስዊዲን የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ሀገር ወዳድ ዜጎች ጋር በመተባበር ሲሆን ሰልፉን የክርስትና እምነት ተከታዮችም በርከት ብለው በመታደም አጋርነታቸውን ገልፀውበታል፡፡

ይድረስ ለክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ



Click here for PDF

ይድረስ ለክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ለጤናዎት አንደ ምን አሉ ፣ እኔ በጣም ደኅና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን ፤ በሎስ አንጀለስ ከየሁዎት ወዲህ በኢትዮ ሚዲያ እንዲሁ በጽሑፍዎ አየሁዎት ፤ ጽሑፉን ሳየው ማመን አቅቶኝ ሌላ ሰው በእርሰዎ ስም የጻፈው መስሎኝ ነበር ፤ ሁኖም ደጋግሜ ካነበብኩት በኋላ የእርሰዎ መሆኑን አወቅሁ ፤  ምንም እንኳን በስም በእድሜና በዕውቀት ባልመስለዎትም ዝም ማለት ግን ተገቢ መስሎ አልታየኝም ። በመሆኑም መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ ። ክቡርነተዎ በጻፉት ላይ ተመሥርቼ ምን መልእክት ሊያስተላለፉ እንደ ፈለጉ ባላውቅም ይህ አካሄድ አንድ ነገር ካልተባለ በትልቅ ስምዎ ሊያስተላለፉት የፈለጉትን ሐሳብ በጎ ነገር ሁኖ አላገኘሁትም ፤ ሆን ብለው ሊክዱትና ሊያስክዱት የፈሉጉት እውነት ስለ አለ እውነቱን ማሳወቅ ግድ ይላል እና ብዙኃኑን ከስህተት ለመጠበቅና  እርስዎንም ለማስታወስ ስል ይህንን መልስ ጽፌልዎታለሁ ።
መግ
ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ምክንያት የሆነው በክቡርነተዎ ተጽፎ በኢትዮ ሚድያ የተለቀቀው ሁለት ባሕርይ ያለው ጽሑፍ ነው ።
አንደኛው ባሕርዩ ጽሑፉ ውዳሴን ከዘለፋ ጋር ፥ ከፋፋይነትትን ከአንድነት ጋር ቀላቅሎ ፥ ምርቅና ፍትፍት ዓይነት ይዘት እንዲኖረው አድርገው ቀምመውታል ። በእውነት ክቡርነተዎ ይህን ጽሑፍ ሲጽፉ በሰከነ አእምሮ የጻፉት አይመስልም ፤ ከሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር የግል ቅራኔ ኑሮዎ ያን ለማስፋፋት ፥ ወይም ቅዱስ ሲኖዶስ ለንድነትና ለሰላም ያቀረበውን ጥሪ ለመበከል ያለመ መሆኑን የጽሑፉ አንደኛ ባሕርይ ያመለክታል ።
ሁለተኛው ባሕርዩ  የኢትዮጵያውንን የፖለቲካ አስተሳሰብ አልደግፍም በሚል ወዳጆቸዎን ያሳሰቡበትን ባሕርይ ይወክላል ። በስደተኛው ፓትርያርክና በሚመሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ላይም ከአሳዳጆቻቸው የተረፈውን ከልክ ያለፈ ዘለፋ ሰንዝረዋል ። የዚህ መልስ ሰጭም በወቅቱ በስብሰባው የነበር ሰው ስለነበር ሳያውቁና ሳይፈቅዱ ሲኖዶሱን እንዲቀበሉ ያደረገዎ መሆኑን አንድን ኣባት በስም ጠርተው ስለ ጻፉ ከዚህ የሚከተለውን መልስ ለመስጠት አስፈለገ ።
ጽሑፉ ክቡርነተዎንም ሆነ ደጋፊዎቸዎን (ገለልተኞችን ወያኔዎችን) እንዲያስተምር እንጂ እንደማያሳዝን ተስፋ በማድረግ ፥ ግን ብዙኃኑን ከስሕተት ለመጠበቅና እውነቱን ለማሳወቅ ብቻ  የተጻፈ ነው ።

Sunday, 17 March 2013

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ! (ደብዳቤያቸውን ይዘናል)



(EMF) በዛሬው እለት መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት፤ የግራዚያኒን ሃውልት መሰራት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል።  ከታሰሩት መካከል ታዋቂው  የህግ ሰው ዶ/ር ኃያዕቆብ ኃይለማርያም ይገኙበታል።
ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹ ከሁለት ቀናት በፊት የአዲስ አበባ አስተዳደር ጉዳዩን እንዲያውቅ በደብዳቤ ገልጸዋል። “…በቅርቡ የኢጣሊያ መንግስት ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ በማርሻል ግራዚያኒ ስም የመታሰቢያ ሙዚየም እና መናፈሻ መስራቱን በመቃወም ሰልፍ ጠርተናል። ስለዚህ የከተማው አስተዳደር ይህንን አውቆ በእለቱ የሚያስፈልገውን ትብብር እንዲያደርግልን እንጠይቃለ።” የሚል ደብዳቤ አስገብተው ነበር። ሆኖም መንግስት ትብብር ከማድረግ ይልቅ የሰላማዊ ሰልፉን አስተባባሪዎች እስር ቤት ወርውሯቸዋል። ለመረጃ እንዲሆን ለአዲስ አበባ አስተዳድር የላኩትን ደብዳቤ ለህትመት አብቅተነዋል።

ሰንሰለቱም ይጠብቃል፤ እርግጫውም ይከፋል …ካልተነሳን!


ሉሉ ከበደ
አስተዳደር በየፈርጁና በየደረጃው፤ ከብሄራዊ መንግስት እስከ ታች የቀበሌ አመራር በመጥፎም ይሁን በደግ መልኩ በዜጎች ህይወት የለት ተለት እንቅስቃሴና አኗኗር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ እንደሚኖረው ሁሉም ሰው እየኖረው ስለሚያየው ማስረጃ መደርደር ላያስፍልገው ይችላል።
በሀገርና በህዝባዊ ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ እናም ውሳኔውን በማስፈጸም ሂደት ላይ ዋናው ተዋናይ በመንግስትነት የተሰየመው አካል ሲሆን፤ እንደየ ሀይላቸውና ቅቡልነታቸው፤ በመንግስት ውሳኔ ላይ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉ ወገኖች መኖራቸው የተለመደ ነው። ለምሳሌ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የሰራተኛ ማህበራት፤ የገበሬ ማህበራት፤ የሙያ ማህበራት፤ ተደማጭ ግለሰቦች እናም አለም አቀፍ ሀይላት፤ የመገናኛ ብዙሀን፤ የገንዘብ ተቋማት፤ ወዘት……ከሁሉም  በላይ ደግሞ ሕዝብ!!..ዲሞክራሲ ባለበት ሀገር ውስጥ በመንግስት ውሳኔ ላይ ተጽእኖ ማሳደር ይችላሉ።
ወደእኛ ሀገር ጉድ የመጣን እንደሆነ በተለይም በደርግና በዘረኛው የወያኔ አስተዳደር ዘመን ፍጹም በሆነ ወደር ያልተገኘለት አንባገነንነት ስር በመውደቃችን፤ የምንታገልለትና የምንመኘው ዲሞክራሲ ጭላንጭሉም እስከወዲያኛው በመጥፋቱ፤ እንኳን የፖለቲካ ድርጅት፤ እንኳን የሙያ ማህበር፤ ህዝብ በነቂስ ከቤቱ ወጥቶ አደባባይ ውሎ አድሮ አቤቱታ፤ሮሮም ሆነ ተቃውሞ ቢያሰማ ወያኔ ከጥፋት አቋሙ ፍንክች እንደማይል ለኢትዮጵያ ህዝብ በተግባር አሳይቷል። ሙስሊም ወንድሞቻችን ከአመት በላይ በሰላም እየታገሉለት ያለው የሀይማኖት ነጻነት ምላሽ ማግኘት ቀርቶ ጭራሽ ይህን አንገብጋቢ ህዝባዊ ሰብአዊ ጥያቄ ወደ ወንጀልነት ቀይሮ፤ ንጹሀን ዜጎችን ወህኒ መቀመቅ ለማጎር ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እየተመለከትን ነው አዲስ ነገር ባይሆንም።
የሙስሊም ወንድሞቻችን ትግል አርአያነቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በእልህና በድንቁርና ለሚታመሰው ለሚተራመሰው አለም በሀገራችን ቢሳካም ባይሳካም እየሞቱ እንዴት ሰላምን ማምጣት እንዴት መብትና ንጻነትን ማስከበር እንደሚቻል የሚያስተምር አጋጣሚ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ይህንን የሙስሊማን ወርቃማ የትግል ስልት ለመቀላቀል የዘገየበት ምክንያቱ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ሰላማዊ ትግል መርጠናል የሚሉን የፖለቲካ ድርጅቶች ደጅም ሆነ እቤት ያሉት፤ ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ትግል ምን አለ ብለው ይሆን የራሳቸው አንሶ ህዝቡንም ይዘው የተኙት? ኢትዮጵያ የሙስሊምና የክርስቲያን ሀገር አይደለችም እንዴ? ፖለቲከኞች እስላም ወይ ክርስቲያን አይደሉም እንዴ?…ጥያቄው እኮ የመብት የነጻነት ነው?….የአምልኮ ነጻነት… የፖለቲካ ነጻነት….የኢኮኖሚ ነጻነት….የመኖር ነጻነት… የመደራጀት…..የመሰብሰብ….ሁሉም ልንታገልላቸው የሚገባ ሊኖሩን የሚገቡ የህይወት እሴቶች፤ እስትንፋሶች ናቸው።

በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች



የጋምቤላ “አኬልዳማ” እየተደረሰ ነው
crime scene 1


በጋምቤላ የመከላከያ ሰራዊት ከጨፈጨፋቸው ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው አቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ ለማጣራት ከአሜሪካ መንግስት የተላኩት የፎረንሲክ (ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉ) ባለሙያዎችን ጋምቤላ ገብተው የማጣራት ሥራ ጀምረዋል። “የጋምቤላ አኬልዳማ” እየተዘጋጀ እንደሆነም ተሰማ።
የጎልጉል የጋምቤላ መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጋምቤላ የደረሱት የአሜሪካ ዜጎች የሄዱበትን ጉዳይ ለማከናወን ከክልሉና ከመከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ዘንድ እክል ገጥሟቸው ነበር።
(ፎቶው የማሳያ ነው)
የፎረንሲክ ባለሙያዎቹ የዜጋቸውን አሟሟት መንስኤና የጉዳት መጠን ለማጣራት ጋምቤላ እንደደረሱ አስከሬኑ በስውር የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ እንደሚፈልጉ፣ አስከሬኑ ላይ የዲኤንኤ ምርመራ በማካሄድ የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ፣ የጉዳቱን መጠንና በምን ያህል ጥይት እንደተደበደበ ለማጣራት፣ ከዚያም በላይ ለምርመራ ስራቸው ይረዳቸው ዘንድ የሚፈልጉትን መረጃ ለመሰብሰብ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ መሄድ እንደሚፈልጉ ጠይቀው እንደነበር ለክልሉ መንግስት ቅርብ የሆኑ ለጎልጉል ገልጸዋል።
ጥያቄውን መቀበል የተሳናቸው የመከላከያና የክልሉ ባለስልጣናት አስከሬኑ መመርመር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን፣ ከተቀበረ የቆየ በመሆኑ ለማውጣት አስቸጋሪ እንደሆነና እንደማይቻል ለመርማሪዎቹ ገልጸው ነበር። “ስራው የኛ ነው” ያሉት መርማሪዎቹ አስከሬኑ በየትኛውም ደረጃ ላይ ቢገኝም ማየት እንደሚፈልጉ፣ ይህ አቋም እንደማይቀየር መሆኑን አመልክተው አስከሬኑ የተቀበረበት ቦታ ደርሰው የሚፈልጉትን ምርመራ ማድረጋቸው ታውቋል። አከራካሪ የነበረውና ግድያው የተፈጸመበት ቦታ የመጓዙ ጉዳይ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጭ፣ የቀረበው መልስ አስገራሚ እንደነበር ይገልጻሉ።

በሚዲያ መረሳት ያስፈራል



“ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”
the meeting


“ከምድር በታች ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰሩትን በቀን ለ10 ደቂቃ እናያቸዋልን። ልብ የሚነካ ነው። የብርሃን ማነስ አይናቸውን እንደጎዳቸው ያስታውቃሉ … ሴቶችን በተገኘው ሰበብ ያስሯቸዋል። ምክንያት ፈልገው እስር ቤት ይከቷቸዋል። ከዚያም ይደፍሯቸዋል። በርካታ የተደፈሩ እህቶች አሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግሥት ያሰማራቸው ሚሊሻዎች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት እንደፈጸሙ ተነግሮናል” ይህ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ፣ ችግሩ ባለበት ቦታ ተገኝቶ የነበረው ስዊድናዊ የፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ማርቲን ካርል ሻቢዬ ቃል ነው።
ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት መስማት ይጨንቃል። ሰዎች በሲቃ የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ለጆሮ  የተለመደ ነው። ከመሬት በታች የጨለማ ክፍል አለ። በዚህ መታጎሪያ ውስጥ ሆነው ስቃይ የሚፈራረቅባቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ማዕከላዊ ብዙ ጉድ ያለበት ሲኦል ነው። የሰው ልጆች በግፍ ማቅቀውበታል። እየማቀቁበትም ነው። ለውጥ እስከሌለ ድረስ የሚቆም አይመስልም። በመሃላ የሚነገርለት ውርስና ይቀጥላል የሚባለው የመለስ ራዕይ አንዱ ክፍል ይህ ነው።
መጋቢት 3፤2005 (3/12/2013) በኖርዌይ ኦስሎ የሥነጽሁፍ ቤት (ሊትሬቸር ሀውስ) በተዘጋጀ የመወያያ መድረክ ላይ ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር። መድረኩን ያዘጋጀው ደግሞ NOAS በሚል ስያሜ የሚታወቀው የስደተኞች ተሟጋች ድርጅት ነው። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አን-ማግሬት ኦስቴና ሁለቱን እንግዶች ካስተዋወቁ በኋላ መድረኩን እየመሩ ውይይቱ ተካሄደ። በዚህ ውይይት ላይ ሁለቱ ጋዜጠኞች እየተፈራረቁ የደረሰባቸውንና በትክክል ያዩትን አስታወቁ።
ማርቲን ካርል ሻቢዬና ባልደረባው የፎቶ ጋዜጠኛ ጆሃን ካርል አበክረው የሚናገሩት ስለ ሙያቸው ነው። “ጋዜጠኛ ለመጻፍ ማየትና ማነጋገር አለበት። በተለያዩ አገራት ጋዜጠኞች ችግር ባለባቸው ቦታዎች ገብተው ለመዘገብ ድንበር ያቋርጣሉ። አሁን በሶሪያ፣ ቀደም ሲል በሊቢያ የሆነው ይህ ነው። በኢትዮጵያ ግን ሽብርተኛ ያሰኛል” ሲሉ ግርምታቸውን ይጀምራሉ።

Friday, 8 March 2013


እኛ ካልረዳን ማን ? አሁን ካልሆነ መቼ ? ከሰሜን አሜሪካ የፍኖተ ጋዜጣ ዝግጅትድጋፍ አስተባባሪ ኮሜቴ

March 7, 2013 11:00 am
  • digg
  • 0
     
    Share
አገር ዉስጥ ለበርካታ ወራት ስትታተም የነበረችዉና በሕዝብ ዘንድ ታላቅ ተወዳጅነትን ያተረፈችዉ፣ የፍኖት ጋዜጣ፣  በአገር ዉስጥ መታተም ካቆመች ብዙ ሳምንታት አሳልፋለች። አገር ቤት ያሉ ማተሚያ ቤቶች በሙሉ፣ ከኢሕአዴግ በተሰጣቸው መመሪያ፣  የፍኖት ጋዜጣን ለማስተናገድ ፍቃደኛ አልሆኑም። ኢሕአዴግ «የኢትዮጵያ ህዝብ መስማትና ማንበብ አለበት» ከሚላቸዉ ዜናዎችና ሃተታዎች ዉጭ የተለዩ ሌሎች የፖሊሲ አማራጮች እንዲስተናገዱ አይፈልግም።
መረጃ ኃይል ነዉ። ከዉጭ በቴለቭዥንና በራዲዮ የሚገኙ፣ ከኢሕአዴግ ገለልተኛ የሆኖ ዜናዎች የታፈኑ ናቸዉ። በርካታ ድህረ ገጾች ታግደዋል። በፌስ ቡክ፣ ትዊተር  በመሳሰሉት ሕዝብን ማደራጀት እንዳይቻል፣ የቴሌኮሚኒኬሽን ተቋማትን በመቆጣጠር ሕዝቡ በኢንተርኔት መረጃ እንዳይደርሰዉ ተደርጓል። የሚያሳዝነው የኢንተርኔት አገግልግሎት ተጠቃሚ የሆነው የሕዝባችን ክፍል ከ0.5 በመቶ በታች መሆኑ ነው።

የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች ልጆቻቸውን ጉዲፈቻ ለመስጠት እየተማጸኑ ናቸው



  • digg
  • 93
     
    Share
Guraferda
የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች
ከደቡብ ክልላዊ መንግስት ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በመፈናቀል ላይ ያሉ ዜጎች ልጆቻቸውን በጉዲፈቻ የሚወስድላቸው አካል እንደሚፈልጉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታወቁ፡፡
‹‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡›› የሚሉት እነዚህ ዜጎች “በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ ከኖርንበት መሬት ተፈናቅለናል፡፡ ከአውሬ ጋር እየታገልን ያለማነውን መሬት ተነጥቀናል፡፡ እነሱ የሚሉን እናንተ አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል መኖር አትችሉም፡፡ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ይሉናል፡፡ አማራ ክልልን እንኳን ሰርተን የምንበላበት መሬት ቀርቶ ጎጆ ቀልሰን የምንኖርበት ቦታ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ፡፡

Tuesday, 5 March 2013

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ



የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (http://www.goolgule.com/)
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።
Gambella
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ



የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው
fisherman
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ። ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።