Monday, 13 January 2014
Sunday, 12 January 2014
ማገዶ!
… አንተ ምን አለብህ ሁልጊዜም ነዲድ ነህ
ለኋላህ ተከታይ ቋያና ሀዲድ ነህ።
ትኩስነት ዕዳ ….
የማገዶ ፍዳ ….
ከሥርጉተ ሥላሴ
እውነት ለመናገር ከዬካቲት በፊት በአጭር ጊዜ ላልመለስ ወስኜ ነበር። ብቻ እንዲህ ሆነላችሁ … ተክዤ ቆዬሁ። አፍጥጬም አዬሁት።
የሬሳው ስንብት (ነብዩ ሲራክ)
እጣ ፈንታ …
ዘመኑ በፈቀደው የአረብ ሃገር ስደትን በኮንትራት ስራ የሳውዲን ምድረ በዳ የባለ ጸጎች ሃገር የረገጠከው ራስክን ደግፈህ ፣ ወላጅ ቤተሰብ፣ ዘመድ አዝማድ ወገኖችህን ለመደገፍ ነበር ። በሳውዲ ቆይታህ በትዕግስት ስታልፍ ያስብከውን ሁሉ ባይሳካም ጋብቻ መስርተህ ሌላዋን የኮንትራት ሰራተኛ ስደተኛ እህትክን ባንድ አቅፈህ ፣ ራስክን በሙያ አንጸህ የተረጋጋ ኑሮን በመኖርህ ላይ እንዳለህ ሳታስበው በውስጠ ደዌ በሽታ ተወጋህ ! ክፉውን ሁሉ የስደት ህይወት በትዕግስት ገፍተህ ደስተኛ ሆነህ ኑሮን ትገፋ እንደነበር አህትህና ባለቤትህ ቅሪት ገላህን ወደ ሃገር ለመሸኘት ለስንብት ስንጓዝ አጫውተውኛል። ፎቶህን አይቸ በህይወት ዘመንህ በአንድ አጋጣሚ አውቅህ እንደነበር ሳውቅ ደነገጥኩ ፣ ድንጋጤየን ዋጥኩት ! ነፍስህን ይማረው ወንደም አለም

ስንብት …
ወደ አልሰሜ እናትና ዘመድ አዝማድ የሚላከውን በድን አካልክን ለመሰናበት በሔድንበት አጋጣሚ በዚያው የሬሳ ማቆያ ጽህፈት ቤት ሃላፊውን ስንት የኢትዮጵያውያን ሬሳ አለ ብየ ጠየቅኩት ። የደስደስ ያለው አረብ ሲመልስ ” አሁን እንኳን ብዙ አይደሉም ፣ ከዚህ በፊት ብዙ ነበር ። እዚህ ማቆያ ውስጥ ፈላጊ ያልመጣላቸው ከአስር የማያንሱ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኛል!” ሲል ዘርዘር አድርጎ መለሰልኝ ። ጠያቂ ስለሌላቸው ፣ ስማቸው ስላማይገኝ ሬሳዎች እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የሬሳው ማንነት ታውቆ የሚያስቀብር ጠያቂ ከጠፋ በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ እንደሚቀበሩ ያጫወተኝ … ሊሰሙት የሚከብድ እውነት !
ወደ አልሰሜ እናትና ዘመድ አዝማድ የሚላከውን በድን አካልክን ለመሰናበት በሔድንበት አጋጣሚ በዚያው የሬሳ ማቆያ ጽህፈት ቤት ሃላፊውን ስንት የኢትዮጵያውያን ሬሳ አለ ብየ ጠየቅኩት ። የደስደስ ያለው አረብ ሲመልስ ” አሁን እንኳን ብዙ አይደሉም ፣ ከዚህ በፊት ብዙ ነበር ። እዚህ ማቆያ ውስጥ ፈላጊ ያልመጣላቸው ከአስር የማያንሱ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ይገኛል!” ሲል ዘርዘር አድርጎ መለሰልኝ ። ጠያቂ ስለሌላቸው ፣ ስማቸው ስላማይገኝ ሬሳዎች እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን የሬሳው ማንነት ታውቆ የሚያስቀብር ጠያቂ ከጠፋ በማዘጋጃ ቤትና በፖሊስ እንደሚቀበሩ ያጫወተኝ … ሊሰሙት የሚከብድ እውነት !
የቀደምቶቹን ወንጀል ለማጋለጥ መቃብር ሲምስ የኖረው ወያኔ በራሱ ጦር ካምፕ ውስጥ የተገኘውን አስከሬን መደበቅ ለምን አሰፈለገው?

አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።
በእንዲህ አይነት ጭካኔ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መገኘት በመንግሥት ተብየው አካል ካለመገለጹም በላይ ግቢውን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው 3ኛ ክፈለ ጦርም ሆነ በግብር ከፋይ ገንዘብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን እስከዛሬ አንድም ቃል መተንፈስ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን እጅግ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስገርምም አድርጎታል። ይባስ ተብሎም በመንገድ ሥራ ቁፋሮው የበለጠ አስከሬን ሊወጣ ይችላል በሚል ስጋት አካባቢው በፖሊስ እንዲታጠር ከተደረገ በኋላ ሥራውም እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?
(ግርማ ሞገስ)

ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው። ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው አገራቸውን ለመርዳት ወደ አገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ (1886-1919) ሁሉ የቁጭት ጥያቄ ነበር። በጣት የሚቆጠረው የነገብረ ሕይወት ትውልድ የውጭ ትምህርት ቀስሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ባፄ ምኒልክ ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ ለዘመናዊነት በር የተከፈተው ባፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን እንደነበር፣ በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1942 ዓመተ ምህረት (እ.ኤ.አ. 1950) የአዲስ አበባ የተፈጥሮና የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ መከፈቱን፣ ኮሌጁ የተደራጀው በኢትዮጵያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት በንቃት ይሰሩ በነበሩ ካናዳውያን እየሱሳውያን (Jesuits) ሲሆን የተማሪዎቹ ቁጥር ከ100 በታች እንደነበር ክፍሉ ታደሰ (The Generation, p. 15-16) ያመለክታል። እሱም ቢሆን እጅግ ዘግይቶ የመጣ በውቅያኖስ ላይ ያረፈ ትንሽ ጠብታ ያህል ነበር። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Subscribe to:
Posts (Atom)